በዩንቨርሲቲው የድጋፍ አገልግሎት በኦፕንና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ ምድብ ዘርፍ የሚገኙ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ሌሎች ሰራተኞች በተገኙበት ታህሳስ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከላይ በርዕሱ የተጠቀሰውን ጉዳይ በተመለከተ 29 ተሳታፊዎች የተገኙበት የግማሽ ቀን ውይይት ተካሄዷል፡፡

የውይይት መነሻ ነጥቦች በቢዝነስና አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ቀርበዋል፡፡

ለውይይት የቀረቡት ፍሬ ሃሳቦችም  ራዕይ ፣ተልዕኮ እና ዕሴቶች፣ ተቋማዊ ሀብቶች፣የድጋፍ ሰጭው ሰራተኛ ስምሪትና ልማት ፣የሥራ መዘርዝር፣ የደንበኞች አገልግሎት ፣የዕቅድ ዝግጅትና አተገባበር እና የአገልግሎት ክፍሉ ለአካዳሚክ ሥራው ስኬት የሚያበረክተው አስተዋፅዎ የሚሉ ናቸው፡፡

በቀረቡት ጉዳዮችና በተሰጠው ማብራሪያም አባላት በከፍተኛ ንቃት የተሳተፍበት ውይይት ተካሔዷል፡፡

ከተሳታፊዎች በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ከመደረጉም ባሻገር መሰል መድረኮች እየተደጋገመ ለሁሉም ቢዳረሱ የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡