በዩንቨርሲቲው የድጋፍ አገልግሎት በዋና መ/ቤት ምድብ ዘርፍ የሚገኙ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ሰራተኞች በተገኙበት ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከላይ በርዕሱ የተጠቀሰው ጉዳይ በተመለከተ ውይይት ተካሄዷል፡፡ 

ለውይይት መርሐ ግብሩ መነሻ ነጥቦች በቢዝነስና አስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት የቀረበ ሲሆን በውይይቱም 24 ተሳታፊዎች ተገኘተዋል፡፡

በውይይቱም የተነሱት ፍሬ ሃሳቦች የተቋሙን ራዕይ ፣ተልኮ እና ዕሴቶች፣ ተቋማዊ ሀብቶች፣የድጋፍ ሰጭው ሰራተኛ ስምሪትና ልማት ፣የሥራ መዘርዝር፣ የደንበኞች አገልግሎት ፣የዕቅድ ዝግጅትና አተገባበር እና የአገልግሎት ክፍሉ ለአካዳሚክ ሥራው ስኬት የሚያበረክተው አስተዋፅዎ በሚሉ ጉዳዩች ማብራርያ እየተሰጠ ውይይት ተካሔዷል፡፡ 

በውይይቱም በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ከመደረጉም ባሻገር መሰል መድረኮች ለሁሉም ቢዳረሱ የሚሉ አስተያየት ተሰጥተዋል፡፡